ማዕከሉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ላበረከተው አስተዋፅኦ የእውቅና ሰርትፊኬት ተበረከተለት

መጋቢት 12/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ማዕከል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ላበረከተው ጉልህ አስተዋፅኦ የምስጋና እና የእውቅና ሰርትፊኬት ከታላቅ ክብር ጋር ተበርክቶለታል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ውጤታማ በሆነ መንገድ እና በተቀናጀ መልኩ ለመከላከል እንዲሁም ብዙ ጉዳት ሳያደርስ ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ባለድርሻ አካላት ውስጥ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አንዱ ነው።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት አካዳሚው፤ ማዕከሉን ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ለይቶ ማቆያ እና ማከሚያነት ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀዱ ላለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ማዕከሉ ወደ ነበረበት አገልግሎት እንዲመለስ መደረጉም ለአካዳሚው ማስረከባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡