ምሁራን ለሀገር ሰላምና ግንባታ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) ምሁራን ኃላፊነታቸውን ተረድተው ለሀገር ሰላምና ግንባታ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ።
የተገኘውን ለውጥ ለማስቀጠልና የሀገር ሉዓላዊነትም ተከብሮ እንዲቀጥል ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል።
በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የምሁራን የምክክር መድረክ እየተካሄደ ሲሆን ለሀገር ለውጥና እድገት የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው ተብሏል።
በተለይ በዚህን ወቅት ሀገር በተለያዩ ከውስጥና ከውጭ ሀይሎች በመነጩ ፈተናዎች እየተፈተነች ትገኛለች የተባለ ሲሆን እኚህን ፈተናዎች በድል በመወጣት ወደፊት እንድትራመድ ምሁራን ከፍተኛ ሚና መጫወት እንዳለባቸውም ተነግሯል።
ይህን ለማድረግም በመቀራረብና በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በታምራት ደሊሊ