ምክር ቤቱ ከፈረንሳይና ከጣሊያን መንግስታት ጋር የተደረጉ የመከላከያ ስምምነቶችን አጸደቀ

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፈረንሳይና ከጣሊያን መንግስታት ጋር የተደረጉ የመከላከያ ስምምነቶችን አጸደቀ።

ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዓመት 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ከፈረንሳይ መንግስትና ከጣሊያን መንግስት ጋር የተደረገውን የመከላከያ ትብብር ስምምነት አስመልክቶ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ ስለስምምነቶቹ ጠቀሜታ አስረድተዋል።

በተጨማሪ ፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ያቀረበውን የተለያዩ ተቋማትን የ2012 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ግኝት ሪፖርት እያዳመጠ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።