ምክር ቤቱ የቀረበለትን የፌዴራል መንግስት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

ጥር 20/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባው የቀረበለትን የፌዴራል መንግሥት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።
ምክር ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን በ9 ተቃውሞ፣ በሰባት ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ነው ያፀደቀው፡፡
ከበጀቱ 90 ቢሊየን ብር ለመከላከያ፣ 8 ቢሊየን ብር ለዕለት ደራሽ እርዳታ፣ 8 ቢሊየን ብር ለመጠባበቂያ፣ 7 ቢሊየን ብር ለካፒታል በጀት እንዲሁም 9 ቢሊየን ብር ለታክስ ጉድለት ማስተካከያ ማፅደቁ ታውቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው ልዩ ስብሰባው የማኅበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድህን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡
በትዕግሥት ዘላለም