ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ እጩዎችን ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም ሹመቱን አጽድቋል።

በዚህም መሰረት

1ኛ. ቀንዓ ያደታ (ፒኤችዲ) የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ሃላፊ

2ኛ. ምትኩ አስማረ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

3ኛ. ሊዲያ ግርማ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ

4ኛ. ሃቢባ ሲራጅ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ሃላፊ

5ኛ.ጀማሉ ጀንበር (ፒኤችዲ) የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር

6ኛ. ጀማል ረዲ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

ሆነው እንዲሾሙ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱ የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።

ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።