ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ

ጥቅምት 25/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፀደቀ።
አዋጁ ለ6 ወራት ተፈፃሚ የሚሆን ነው፡፡
በአገር ኅልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/14ን ያፀደቀው ምክር ቤቱ የአዋጁን አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ እየመከረ ነው፡፡