ምክር ቤቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመት አጸደቀ

ጥር 9/2015 (ዋልታ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ቴዎድሮስ ምሕረት ከበደን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ በ3 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ሹመታቸውን ያጸደቀው።

በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አበባ እምቢአለ በሙሉ ድምፅ ሹመታቸውን ያፀደቀ ሲሆን ተሿሚዎችም በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡