ምክር ቤቱ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል

መጋቢት 14/2013 (ዋልታ) – 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የምክር ቤቱን 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡