ም/ቤቱ የበይነ መንግሥት ፊሲካል ግንኙነት ቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ እየተወያየ ነው

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የበይነ መንግሥት ፊሲካል ወይም የወጪ እና ገቢ ግንኙነት የሚመራበት አሰራርና ቀጣይ አቅጣጫን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
በዚህም ባለፉት 30 ዓመታት የክልሎች የወጭና ገቢ ግንኙነቶች ምን ይመስላሉ በሚለው ጉዳይ እና በቀጣይ አቅጣጫዎችም ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ግንኙነቱ የበጀት አለመመጣጠንን ለመቅረፍ ከማገዝ ባለፈ የክልሎችን የአቅም ውስንነት በመመልከት ወጭ እና ገቢን ተመጣጣኝ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በመድረኩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመስከረም ቸርነት
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!