ም/ቤቱ የቴሌኮም አገልግሎት ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ

ግንቦት 14/2013 (ዋልታ) – የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ፈቃድ እንዲሰጥ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ማፅደቁን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡
“የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታሪካዊ ውሳኔ ወስኗል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
“ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ ላቀረበው ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ አጽድቋል” ብለዋል፡፡
በአጠቃላዩ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የሙዓለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዲኖረው ያደርገል ብለዋል።
ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት የማስገባት ዕቅዳችን ፈር ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ግልጽነት እና ውጤታማነት የሞላበት ሂደት ላሳኩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።