ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሹ ቢን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በመላው አፍሪካ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ ልማትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ የምታበረክተውን ገንቢ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል መመላከቱንም በኢትዮጵያ ከቻይና ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!