ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ነው – ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ስነ ምግባርን እና ሙያተኝነትን የማጠናከር እና በየትኛውም የሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊታችንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፣ በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የተጠያቂነት እና የስነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ስርዓት ርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡