ሩሲያ የአፍሪካ እና እስያ አገራትን አመሰገነች

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) ምዕራባዊያን በሩሲያ ላይ ያልተገባ እና ተቀባይነት የሌለው ማዕቀብ ሲጥሉ የአፍሪካ እና የእስያ አገራት ባለመተባበራቸው ሩሲያ አመሰገነች፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አሜሪካ በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ባለው ጦርነት የያዘቸው አቋም ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

በተለይም አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባዊያን አገራት የጦር መሳሪያ ከመስጠት ጀምሮ ዩክሬንን በመደገፍ በሩሲያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሄዱበት ርቀት ተቀባይት የለውም ነው ያሉት።

በሜሮን መስፍን