ሪያል ማድሪድ ለ14ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

ግንቦት 21/2014 (ዋልታ) ሪያል ማድሪድ ለ14ኛ ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ።

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ስታደ ፍራንስ ላይ የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።

የድል ግቧን ብራዚላዊው ቪኒሽየስ ጁንየር በ59ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር ክለቡን ሻምፒዮን አድርጓል።

ካርሎ አንቸሎቲ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ታሪክ አራት የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት የመጀመሪያው አሰልጣኝም ሆነዋል።

በሀብታሙ ገደቤ