ርዕሠ መስተዳድር ሽመልስ አሶሳ ገቡ

ሐምሌ 24/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ ልዑክ አሶሳ ከተማ ገባ።

ልዑኩ አሶሳ ሕዳሴ አየር ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና በከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።

ልዑኩ በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ላይ ሚሳተፍ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ምርቃት ላይ የሚታደም መሆኑን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡