ርዕሰ መስተዳድሩ የጎንደርን ሰላም ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሠራ ነው አሉ

ሰኔ 5/2014 (ዋልታ) የጎንደርና አካባቢውን የሰላምና የልማት ሁኔታ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስጠበቅ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳስሩ በጎንደር ከተማ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በከተማዋ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ምክክር እያደረጉ ነው።

መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የሕግ ማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው ሰላም ለማደፍረስ የሚሯሯጡ የጥፋት ኃይሎችንም ለሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

የሰላም እጦት በክልሉ ከተሞች የኢንቨስትመንት ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ሕዝብ ለሰላሙ መረጋገጥ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡