ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ

ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በ18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “እንኳን ደስ አላችሁ ጀግኖቻችን፤ ይህንን ቡድን በኩራት፣ በትህትና እና በልዩ ፈገግታ በመምራት ትልቅ ድል ላስመዘገበችው ለአንጋፋዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ልዩ ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል።