ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል ሀዋሳ ገቡ

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጫምባላላ” ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።

ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ አምባሳር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና እንግዶችም በበዓሉ ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።

በሀዋሳ ዶሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW