ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አወገዙ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አገራችንን ከአሸባሪዎች ለማጽዳት የጀመርነውን ዘመቻ አጠናክረን ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለን ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

“በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሸባሪው ሸኔ በንጹሐን ወገኖች ላይ በፈጸመውን ግድያ የተሰማኝን ሀዘን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁ” ሲሉም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW