ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

ሐምሌ 29/2014 (ዋልታ) ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደርን ከመሰረቱት ቀደምት ባለሙያዎች መካከል የነበሩ መሆናቸውንም ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡