ሰለሞን ባረጋ በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አሸነፈ

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) ትናንት ምሽት በተካሄደው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ፡፡
በወንዶች ምድብ በተካሄደው 5 ሺሕ ሜትር የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ሙክታር እድሪስ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በምድቡ አዲሱ ይሁኔ 5ኛ ሆኖ ውድድሩን የጨረሰ መሆኑን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገነኘው መረጃ ያሳያል፡፡