ሰላምን ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) ሰላምን ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ቢሮው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመሆን በክፍለ ከተማው ለሕዝባዊ ሰራዊት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የቢሮ ኃላፊው ቀነአ ያደታ (ዶ/ር) ያለሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ ስለማይቻል ኅብረተሰቡን ተሳታፊ ማድረግ ለሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው ማለታቸው ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዘመኑ ደሳለኝ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማን ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡