ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል ኪልባቲ ዞን በራህሌ ወረዳ የሕወሓት የሽብር ቡድን በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ ድጋፍ አደረገ።
የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) ን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በቦታው ተገኝተው ድጋፉን ለተፈናቃዮች አስረክበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአፋር ሕዝብ ላይ የተጋረጠውን ፈተና በተጠና መልኩ እየፈታ እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲቲው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።