ሰሞኑን አገር ለማፍረስ በድብቅ የተደረገውን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ሰሞኑን የሽግግር መንግሥት ማቋቋም በሚል መነሻ አገር ከሃዲዎች ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር አገር ለማፍረስ በድብቅ ያደረጉትን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ።
ይህ ማዕከል ሰሞኑን በኤፍሬም ይስሃቅ አወያይነት የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደሮችና የአሸባሪው ሕወሓት አባላትና የጥቅም ተጋሪዎች የተካሄደውንና ኢትዮጵያን የማፍረስ ውይይት አዘጋጅቷል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ የሀገርን ኅልውናና ሉኣላዊነት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ የሚጠረጠር የሲቪል ማኅበር ድርጅትን ፈቃድ እንዲሰረዝ ያዛል በሚለው መሰረት የሰላም ልማት ማዕከሉ ፈቃድ ተሰርዟል።
የሲቪል ማኅበረሰቦች ባለስልጣን በጻፈው ደብዳቤ መሰረት የማዕከሉ ፈቃድ ከዛሬ ኅዳር 17 ጀምሮ መሰረዙ ተገልጿል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!