ሰበር ዜና ፤ ጋሸና በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ዋለ

ጋሸና በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ዋለ

ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት ቁልፍ የጦር ስልታዊ ቦታው አድርጎ ይዞት የነበረውና የመሸገበት የጋሸና ግንባር ምሸግ በጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊትና አብረውት በተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ብርቱ ክንድ ተሰብሯል፡፡

በዚህም ይህ ስልታዊ ስፍራ በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ሲገባ አሸባሪው ቡድን መሉ በሙሉ ተደምስሶ ሽንፈትን ተከናንቧል፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እየተካሄደ ባለው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” የወገን ጦር ጋሸናን ከጠላት አፅድቶ ወደ ላሊበላና ወልዲያ እየገሰገሰ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

በወራኢሉና ደጎሎ እንዲሁም በሸዋ ግንባር የወገን ጦር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑንም ነው “ዛሬ ብሩህ ቀን ነው” ሲሉ በጀመሩት መግለጫ የገለጹት፡፡