“ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፈተ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በጅግጅጋ ከተማ ተከፈተ፡፡

በአውደ ርዕዩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ በኃ/ስላሴ፣ በደርግ፣ በኢሃዴግ እና በብልፅግና የስልጣን ዘመን ውስጥ በአገሪቱ የተከናወኑ ተግባራት እና የለውጥ ጉዞን የሚዳስሱ ክንውኖች በፎቶ ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም በአሸባሪው ሕወሓት የተሰው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችና የወደሙ ተቋማት ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

አውደ ርዕዩ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በክልል ደረጃ በጅግጅጋ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ  ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን በቀጣይ በአስር የክልል ከተሞች እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል፡፡

አመለወርቅ መኳንንት(ከጅግጅጋ)