ሸማችና አምራችን የሚያገናኝ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

ጥቅምት 9/2014 (ዋልታ) የንግዱን ዘርፍ በማዘመን ሸማችን ከአምራች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ) ይፋ ሆነ::

በአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ የበለፀገው የኢ-ኮሜርስ ቴክኖሎጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት አካባቢ አምራችን በቀላል እንዲሁም ቀጥተኛ በሆነ መንገድ የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ መሆኑ ተገልጿል::

ቴክኖሎጂው የንግድ ሰንሰለትን በማሳጠር የዋጋ ንረትን በማስቀረት ረገድ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል::

ዘመኑን የዋጀ የግብይት ሥርአትን መፍጠር የንግድ ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ አበርክቶው የላቀ በመሆኑ የኢ-ኮሜርስም የሀገርን ምጣኔ ሀብት የማሳደግ አቅም እንዳለው ከግምት ውስጥ በማስገባት የንግዱ አለም ተዋናዮች ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ተብሏል::

(በሔብሮን ዋልታው)