ቋሚ ኮሚቴዎች በቡራዩ እየተገነባ የሚገኘውን የተሰጥኦ ማዕከል ግንባታ ጎበኙ

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) የመንግሥት ወጪ ቁጥጥርና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሰው ሀብት ልማት ሥራ ከህሎት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቡራዩ እየተገነባ የሚገኘውን የተሰጥኦ ማዕከል የግንባታ ሂደትን ጎበኘ፡፡

ግንባታ ማዕከሉ ከተጀመረ 5 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በፀጥታ ችግር እንዲሁም በተቋራጩ ችግር ምክንያት የግንባታው ሂደት መዘግየቱ ተጠቁሟል፡፡ ሆኖም ግን ችግሩን በመቋቋም ግንባታው ወደ ተሻለ ሂደት እንዲፋጠን ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

የተሰጥኦ ማዕከሉ ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ1 ሺሕ በላይ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል ተብሏል።

በ2015 ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ሥራውን እንደሚጀምር ያስታወቀው ማዕከሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የራሱን እምርታ እንደሚያስመዘግብ አስታውቋል።

በዙፋን አምባቸው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW