በሀረሪ ክልል ከ245 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

የካቲት 18/2015 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ከ245 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

ፕሮጀክቶቹ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የክልሉና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የተመረቁት ፕሮጀክቶችም የመንገድ፣ የትምህርት ቤት፣ የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤት እና የወጣቶች ስብእና ልማት ማእከል ናቸው።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)