በሀረሪ ክልል የቅዳሜ ገበያ የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና እያቀለለ መሆኑ ተገለጸ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) “በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው የቅዳሜ ገበያ የደላሎችን ሰንሰለት በማስቀረት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ እንዲገናኝ አድርጓል” ሲሉ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሚስራ አብደላ ገለጹ።

ገበያው በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ጫናዎች በመቀነስ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።

በቅዳሜ ገበያው አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬና የመኸር ሰብል ምርቶችን በተሻለ አቅርቦትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች እየቀረበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ገበያው በአግባቡ እንዲካሄድና ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አምራች አርሶ አደሮች፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ ደንብ አስከባሪዎች፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም አምራቹ እና ሸማቹ በቀጥታ የሚገበያዩበትን ጤናማ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር የጀመርናቸው መሰል ተግባራት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ማለታቸውን ከከልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።