በህገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ የገጠሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ)

ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ፊንፍኔ ዙሪያ ዞን ለገጣፎ ለገ ዳዲ ከተማ 01 ቀበሌ በተለመዶ ገዋሳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ የገጠሙ ግለሰቦች ከነተባበሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ መሰረት መሆኑም ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከለገ ጣፎ ለገ ዳዲ ፖሊስ መምሪያ በጋራ ባደረጉት ቅንጅት አሰራር እስካሁን ከተቋሙ እውቅና እና አሰራሩ ውጭ ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መንገድ የተገጠሙ 70 ቆጣሪዎች እና ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በአካባቢው ምሰሶዎችን ጨምሮ በማይታወቁ ግለሰቦች የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ገመዶች እንዲሁም ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን በአንድ ግልሰብ ቤት የተጠቀለለና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብርትነት የሚጠረጠር የኤሌክትሪክ ገመድ ተገኝቷል፡፡

በህገ ወጥ ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ቆጣሪ በሚገጥሙበት ወቅት ቆጣሪውን በህገወጥ መንገድ ካስገቡላቸው ግለሰቦች ከእያንዳንዳቸው ከ20 እስከ 35 ሺሕ ብር እንደሚቀበሉ ተገልጿል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!