በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 51,700 ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

የካቲት 13/2013 (ዋልታ) – በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 51 ሺህ 700 የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ገንዘቡ የተያዘው የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም አንድ የህዝብ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጅጅጋ ወደ ሱማሌላንድ ሲጓዝ በተደረገ ፍተሻ ነው።

ህገ-ወጥ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገው ለቶጎውጫሌ ጉምሩክ መቆጣሪያ ጣቢያ በደረሰ ጥቆማ ነው ተብሏል፡፡

የተያዘው ገንዘብ በወቅታዊ ምንዛሪ 2 ሚሊዮን 56 ሺህ 62 ብር ዋጋ ያለው መሆኑን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል።