በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ከነተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተያዙት የጦር መሳሪያዎች ክላሾች፣ ሽጉጦች፣ ቦምቦች፣ ጥይቶችና የመከላከያ ሰራዊት ዩኒፎርሞች እንደሚገኙበት ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡