በሐረሪ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የሥራ ስምሪት ተሰጠ

ጥቅምት 26/2014 (ዋልታ) በሐረሪ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ቀጣይ ሥራዎችን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ስምሪት ሰጥተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በአገር ደረጃ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሻ በማድረግ ለምስራቅ ዕዝ ዋና መምሪያ እና ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ውይይት በማድረግ እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አሽባሪው የሕወሓት ቡድንና ተላላኪው ሸኔ ጋር አገር ለማፍረስ የሞት ሽረት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ እንደሚጠቁመው የጥፋት ቡድኑን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ ኮሚቴው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ሥራውን ማስፈጸም አለበት ብለዋል።