በሕገወጥ መንገድ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበሩ ሽጉጦችና ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

ሚያዝያ 06/2013 (ዋልታ) – መነሻውን ባሕርዳር በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ 108 ሽጉጦችና እና ከ2 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በማንኩሳ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ህገወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ማንኩሳ ከተማ ሲደርሱ ከነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነው የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ያስታወቀው፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ዋና ሳጅን መንገሻ ይማም እንደገለጹት፣ በተካሄደ ፍተሻ ከ2 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች እና 108 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን  ዋና ሳጅን መንገሻ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡