በመዲናዋ ለ229 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የስራ እድል ተፈጥሯል – ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት ለ229 ሺህ 370 ነዋሪዎች አዲስ የስራ እድል መፈጠሩን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ከተፈጠሩት የስራ እድሎች ውስጥም 179 ሺህ ቋሚ ስራ ሲሆን ተጠቃሚ የሆኑት ነዋሪዎች ደግሞ 79 በመቶ ወጣቶች እና 48 በመቶ ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡

የሥራ እድል ፈጠራው አበረታታች ውጤት መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ፣ በከተማዋ ከሚታየው የስራ አጥነት መጠን አንጻር ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅም አመላክተዋል።