በመዲናዋ በህገወጥ መንገድ የተወረሩ 671 ቦታዎች መገኘታቸው ተገለፀ

ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በህገወጥ መንገድ የተወረሩ 671 ቦታዎች ማግኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ጀማል አሊ ገልጸዋል፡፡

260ሺሕ 106 ካሬ ሜትር ይዞታዎች ወደ መንግሥት ባንክ መመለሳቸውንም ተናግረዋል፡፡

በህገወጥ የመሬት ወረራ ተግባር የተሳተፉ 88 በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የነበሩ አመራሮች ከሥራ ገበታቸው መታገዳቸው የተገለፀ ሲሆን አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛልም ተብሏል፡፡

በህገወጥ ወረራ የተያዙት ቦታዎች ካርታቸው ሙሉ በሙሉ መምከኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

መሬትን በህገወጥ መንገድ ለመውረር የሚደረገው ጥረት ከሽብር ቡድኑ አገር የማጥፋት ሴራ ያልተናነስ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ህገ ወጥ ወረራ በስፋት የተስተዋለባቸው ለሚ ኩራ፣ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት