በመዲናዋ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) በመዲናዋ 1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በላም እንዲከበር የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ኅብረተሰቡንና የዕምነቱ ተከታይ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በተሰራው ሥራ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ዙሪያ የተከናወነው የሶላት ሥነ ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሥነ ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የበዓሉ ታዳሚዎች ላሳዩት ቀና ተባባሪነት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ቀሪው የበዓል አከባበር ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል በየአካባቢው በቂ የፀጥታ ኃይል ተመድቦ ተግባሩን እየተወጣ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኅብረተሰቡ ከፀጥታ ጉዳይ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97 መጠቀም ይችላል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW