በረመዳን ፆም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከምግብ ብቻ ሳይሆን ራሱን የሚያርቀው ከመጥፎ ሀሳብና ድርጊትም ጭምር ነው – ር/መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሚያዝያ 23/2014 (ዋልታ) በረመዳን ፆም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ራሱን የሚያርቀው ከመጥፎ ሀሳብና ድርጊትም ጭምር ነው ሲሉ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ለ1ሺሕ 443ኛው ኢድ- አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በፆም ወራት ሰዎችን በገንዘብና በቁስ ከመርዳት ባሻገር በጉልበትና በእውቀት ማገልገል፤ በዘካ ዘልፈጥር ያጡትን የተቸገሩትን ወገኖቻችሁን በማብላት በማጠጣት ምንም ለሌለቸው ያላችሁን በመለገሳችሁ ላመሰግናችሁ አወዳለሁ ሲሉም በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል፡፡