በርካታ ህገ ወጥ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ በመቀናጀት ሰሞኑን 42 የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ባደረገው ፍተሻ በርካታ ህገ ወጥ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች መያዙን አስታወቀ።

ከተያዙ ህገ ወጥ ገንዘቦች ጋር በተገናኘ ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል።

ግለሰቦቹ የብሔራዊ ባንክ መመሪያን በመተላለፍ 1 ሚሊየን 363 ሺሕ 170 ብር፣ በርካታ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን ይዘው መገኘታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።