በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የተመራ ልዑክ በክላስተር የለማ በቆሎን ጎበኘ

ጥቅምት 8/2015 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በክላስተር የለማንፅየበቆሎ ማሳ ጎበኘ።

በተያዘዉ አመት በክልሉ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን መሬት በኩታ ገጠም በቆሎ ምርት መሸፈኑ የተገለፀ ሲሆን 67 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ጌቱ ገመቹ ተናግረዋል።

የአካባቢው አርሶ አደሮች በበኩላቸው ከኩታ ገጠም ምርቱ ተጠቃሚ መሆናችዉን ገልፀው ወደፊትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ፌናን ንጉሴ (ከአዳሚ ቱሉ)