በሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተካሄደ

ነሃሴ 08/2013 (ዋልታ) – በሰሜን ወሎ በፀጥታ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተካሄደ።
በወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ እክል መነሾ ከቄያቸው ለተፈናቀሉ የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ አሰባስበዋል::
ኢትዮዽያዊነት ወንድም ለወንድሙ አለሁ ባይነቱን ማሳያ ነው ያሉት የአካባቢው ተወላጆች ተፈናቃዮቹን ወደ ቀደመ የኑሮ ዘያቸው ለመመለስ የአቅማቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል::
የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ላይ በርካታ እኩይ ተግባራትን ሲፈፅም የቆየው አሸባሪው የህውሀት ቡድን በአሁኑ ወቅትም ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለው ለስደት በመዳረጋቸው እነዚህ ወገኖቻችን መድረስ ደግሞ የእኛ ኢትዮዽያውያን ሀላፊነ ነው በማለት የተጠነሰሰ ሀሳብ ነው ተብሏል::
በሀገር ህልውና ላይ የተቃጣውን የአሸባሪው ሀይል ጥቃት የሀገራቸው ልጆች የሆኑት ኢትዮዽያውያን ለመመከት እንዲሁም እስከወዲያኛው ለማሰናበት በአንድነት መሰለፍ ያሻል ተብሏል::
(በሔብሮን ዋልታው)