በሳዑዲ አረቢያ ችግር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን መመለስ ጀመሩ

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) በሳዑዲ አረቢያ ችግር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር በረራ ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የአቀባበል ኮሚቴው አባላት በቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት መጀመሪያ በረራ ከሪያድ 157 ህጻናትና 341 ሴቶች በድምሩ 498 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።

እንደኢዜአ ዘገባ በሳዑዲ አረቢያ የነበሩ ከ100 ሺሕ በላይ ዜጎች እስከ ቀጣይ 11 ወራት ለመመለስ የተሰወነ ሲሆን ለስደተኞች አቀባበልም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ስደተኞች መልሶ እስኪቋቋሙ ድረስ ጊዜያዊ ማረፊያም መዘጋጀቱ ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW