በሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ጨዋታ ኡጋንዳና ኮንጎ አቻ ተለያዩ


ሐምሌ 11/2013 (ዋልታ) – በሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ኡጋንዳና ኮንጎ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡
በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች እግር ኳስ ውድድር ትናንት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ዛሬ በተደረገው ጨዋታም ኡጋንዳና ኮንጎ ያለምንም ግብ መለያየታቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡