በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩት ፀጋዬ አበበና አስቻለው በላይ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ሁለቱ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ አስረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ባለሀብቶቹ በክልሉ በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡