በሸኔ ሎጅስቲክስ አቅራቢነት በተጠረጠረች ግለሰብ መኖሪያ ቤት ከባድ መሳሪያና ጥይቶች ተያዙ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ ነዋሪ በሆነች እና በሸኔ የሽብር ቡድን የሎጀስቲክስ አቅራቢነት በተጠረጠረች ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከባድ መሳሪያና ጥይቶች ተያዙ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያካሄደውን ክትትልና ጥቆማ ለኦሮሚያ ፖሊስ በሰጠው መሰረት ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር እንድትውል መደረጓ ተገልጿል።
ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ በተጠርጣሪዋ መኖሪያ ቤት ውስጥም በተደረገ ፍተሻ በምስራቅ ወለጋ ዞን ለሚንቀሳቀሰው የሸኔ የሽብር ቡድን ለማቀበል በዝግጅት ላይ የነበረ አንድ ብሬን ከ426 ጥይት እና 10 የብሬን ጥይት ማስቀመጫ ሰንሰለት ጋር እንዲሁም 179 የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ያሳያል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!