በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው የኮሚሽጋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ችግኝ ተከሉ


ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) –
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው የኮሚሽጋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን ባስገነባው ኮሚሽጋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸውና በአካባቢያቸው ችግኞችን መትከላቸውን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡