በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው 13ኛው ትምህርት ቤት በአፋር ተመርቋል

 

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን በየክልሎች ሁሉ ለማስፋትና ለማሳደግ በሚደረገዉ ጥረት የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ቤቱን ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸውና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ መርቀው ከፍተውታል።

በጽህፈት ቤቱ ከተገነቡት 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉን በአፋር ክልል በአዉሲ ራሱ ዱብቲ ወረዳ የተገነባዉን ዱብቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬዉ እለት አስመርቋል፡፡

13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ዱብቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዉስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ የኮምፕዩተር ላብራቶሪ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አሉት፡፡

ጽህፈት ቤቱ በዛሬዉ እለት ያስመረቀዉ ዱብቲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት 13ኛዉ ሲሆን ቀሪዎቹ በዚህ አመት ግንባታቸዉ የተጠናቀቁ ትምህርት ቤቶችን ማስመረቁን ይቀጥላል፡፡
ትምህርት ቤቱ በሁለት ፈረቃ አንድ ሺህ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለዉ፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በዚሁ አጋጣሚ በትምህርት ቤት እርቀትና እጥረት ምክንያት ልጆቻቸዉን ወደ ትምህርት ገበታ የዱብቲ ወረዳ እንዲሁም አዋሳኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ልጆቻቸዉን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እድሉን እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፏል።