በባሕር ዳር እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ውይይት ጥያቄዎች ከማኅበረሰቡ እየተነሱ ናቸው

መጋቢት 14/2014 (ዋልታ) በባሕር ዳር እየተካሄደ ባለው የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባኤ የሕዝብ ውይይት የተለያዩ ጥያቄዎች ከማኅበረሰቡ እየተነሱ ናቸው።

በውይይቱ ከተለያዩ የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል አካባቢዎች ተፈናቅለው ችግር ላይ የወደቁ ዜጎች እጣ ፈንታን በተመለከተ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

በዚህም ፓርቲው እንደ ፓርቲና እንደ መንግሥት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መስራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ታችኛውን አመራር መፈተሸ፣ ለኑሮ ውድነት እልባት መስጠት፣ በፋኖ ጉዳይ የመንግሥት አቋም መታወቅ አለበት ተብሏል፡፡

በክልሉ የመንግሥት ሀብትና ንብረት ብክነት እንዲሁም የሙስና ስር መስደድ ችግሮች በስፋት ተነስተዋል።

ምንይሉ ደስይበለው (ከባሕር ዳር)