በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህልፈት ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል – ጠ/ሚ ዐቢይ

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህልፈት

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው ገለጹ።

ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት የሀዘን መልዕክት በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው፤ ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ ሲሉም አክለዋል። –